Monday, March 1, 2010

ጭቃን አድርቆ ተሻሻለ ማለት ዝናብ እስቲዘንብ ድረስ ነው።

ሰላም ተዋህዶ የተባለው ብሎግ ሰሞኑን በሚጽፈው ጽሁፍ ለህዝብ የተቆረቆረ መስሎ ታይቶ ነበር። እኛም እውነት ለመልካም ተግባርና ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኑን ለማፋቀር የቆመ መስሎን ማመስገን ጀምረን ነበር! ለካስ መልሶ ጭቃ ለመሆን የሚጠብቀው ዝናብ ኖርዋል።

የደጀሰላም ድረገጽ፤ የሐመር እና የስምአጽድቅ ኤዲተር የሆነው በዲሲ ከተማ በግዞት ላይ የሚገኘው የማህበረ ሰይጣን ባልደረባ እና የሚካኤል ሰይፍ የሚያስልፈልፋቸውና የሚያክለፈልፋቸው እኩያን አሳሳቾች እብዙ ውሸት መሀል ትንሽ እውነት በመደብለቅ ሰላምተዋህዶ የሚል ብሎግ ከፍተው ህዝብን ለማሳሳት የሚያደርጉት ጥረት እርቃኑን ስለወጣ አዚማቸው አልይዝ ብሎ ውርደታቸውን እየተጎናጸፉ ይገኛሉ።

የቤተክርስቲያኗ ከሳሾችና ግብረአበሮች ብሎግ ደግሞ መረዋመታ የሚል ስም ተሰጥቶት እንደመዥገር ተጣብቀው የቤተክርስቲያኗን ሀብትና ንብረት ለአመታት ሲዘርፉ የኖሩት እነተኮላ፤ በቀለ፤ ነጋሽ፤ጸሃይጽድቅ፤ ጥሩአየር፤ መስፍን ወዘተ፤ ከነግብረአበሮቻቸው ዛሬ የቤተክርስቲያን ሃሳቢ በመመሰል የመሸታ ቤት አሉባልታቸውን አፋቸውን ሞልተው ለማውራትና ለመዘገብ በቅተዋል። እነዚህ የአርዮስ ልጆች ለሚካኤል ቤተክርስቲያን፤ ጓዳቸውን የቀድሞውን ሊቀመንበር ለመጥቀስ “ለሚጠጡት ሻይና ለሚበሉት ዳቦ ያህል እንኳን ስሙኒ የማይሰጡ” ሲሆኑ አባል ላልሆኑለት ቤተክርስቲያን አሳቢ በመምሰል እንዳይዘርፉ ያስቆሟቸውን ሁሉ በመወንጀልና ስም በመስጠት ይኮንናሉ። የነዚህን ሌቦች ተግባር በዝርዝር የሚያውቁት የሚካኤል ቤተክርስቲያን አባላትም አንቅረው አክ እንትፍ ብለዋቸዋል።