ሰላም ተዋህዶ የተባለው ብሎግ ሰሞኑን በሚጽፈው ጽሁፍ ለህዝብ የተቆረቆረ መስሎ ታይቶ ነበር። እኛም እውነት ለመልካም ተግባርና ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኑን ለማፋቀር የቆመ መስሎን ማመስገን ጀምረን ነበር! ለካስ መልሶ ጭቃ ለመሆን የሚጠብቀው ዝናብ ኖርዋል።
የደጀሰላም ድረገጽ፤ የሐመር እና የስምአጽድቅ ኤዲተር የሆነው በዲሲ ከተማ በግዞት ላይ የሚገኘው የማህበረ ሰይጣን ባልደረባ እና የሚካኤል ሰይፍ የሚያስልፈልፋቸውና የሚያክለፈልፋቸው እኩያን አሳሳቾች እብዙ ውሸት መሀል ትንሽ እውነት በመደብለቅ ሰላምተዋህዶ የሚል ብሎግ ከፍተው ህዝብን ለማሳሳት የሚያደርጉት ጥረት እርቃኑን ስለወጣ አዚማቸው አልይዝ ብሎ ውርደታቸውን እየተጎናጸፉ ይገኛሉ።
የቤተክርስቲያኗ ከሳሾችና ግብረአበሮች ብሎግ ደግሞ መረዋመታ የሚል ስም ተሰጥቶት እንደመዥገር ተጣብቀው የቤተክርስቲያኗን ሀብትና ንብረት ለአመታት ሲዘርፉ የኖሩት እነተኮላ፤ በቀለ፤ ነጋሽ፤ጸሃይጽድቅ፤ ጥሩአየር፤ መስፍን ወዘተ፤ ከነግብረአበሮቻቸው ዛሬ የቤተክርስቲያን ሃሳቢ በመመሰል የመሸታ ቤት አሉባልታቸውን አፋቸውን ሞልተው ለማውራትና ለመዘገብ በቅተዋል። እነዚህ የአርዮስ ልጆች ለሚካኤል ቤተክርስቲያን፤ ጓዳቸውን የቀድሞውን ሊቀመንበር ለመጥቀስ “ለሚጠጡት ሻይና ለሚበሉት ዳቦ ያህል እንኳን ስሙኒ የማይሰጡ” ሲሆኑ አባል ላልሆኑለት ቤተክርስቲያን አሳቢ በመምሰል እንዳይዘርፉ ያስቆሟቸውን ሁሉ በመወንጀልና ስም በመስጠት ይኮንናሉ። የነዚህን ሌቦች ተግባር በዝርዝር የሚያውቁት የሚካኤል ቤተክርስቲያን አባላትም አንቅረው አክ እንትፍ ብለዋቸዋል።
ቢወዱም ባይወዱም አዲስ ቦርድ ተመርጧል። እንኳን የነሱ የመንደር አሉባልታ ወሬ ቀርቶ የነአቶ ሃይሉ እጅጉና የድሮው ሊቀ መንበር የብዝበዛ ተባባሪወች ምርጫዉንና ሽግግሩን ለማቆም አልቻሉም።
የባሰዉን ቅሌት የተሽከመው ዋና ጸሃፊ የነበረውና እራሳቸው አቶ እዩኤል ከሂሳብ ሰራተኛው ጋርና ሽግግሩ ይቁም እያሉ ሲጮሁ የነበሩት አቶ ሃይሉ አጅጉ ያሰለፋቸው አሽከሮች በይፋ ተጋልጠዋል። ውሸት የማይሰለቸው ዋና ጸሃፊ የነበረው እንደ ልማዱ በሃሰት ሲመሰክር ውሏል። ሰነድ ከኮምፒተር ዉስጥ አልደለዝኩም መደለዝ የቀረው ብዙ ገንዘብ በልቶ ያስበላው ዲያቆን በነበር ጊዜ ነው ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። የማጭበርበር ጓደኛው ኦዲተር የነበሩት ወይዘሮ ግን ካሁን ቀደም በቅርቡ አዎን ደልዣለሁ ሲሉ ከመሰማታቸውም በላይ መደለዝ እንዲከለከል ከተስማሙት ቦርድ አባላት አንደኛዋ ነበሩና በዚህም አቅጣጫ በቅርቡ ገንዘብ ተከፍሎት የመጣ ሰነድ ማንም ተነስቶ እንዳይቀይር ያደረገ የአቶ አለማየሁ ተቀጣሪ ነበር፡ ይህም የሆነው ባለፉት 3 ወራት ውስጥ ነው።
ያሁኑ የሂሳብ ሹምም እንደገለጡት የመደለዣ እገዳ ከተደረገ ገና ሶስት ወር እንዳልሞላው ሲያስረዱ ማንም ሊያዳምጣቸዉና ሊሰማቸው አለመፈለጉ በግልጽ ታይቷል። በሌላውም የሃሰት ምስክርነቱ የአባላቱ ሃያ አምስት መቶኛ ስለመጣ ኮረም ሞልቷል በማለት ላድማጩ ግራ የገባ ነገር ሲናገር እያየን ማንም ገና አልሞላም ያለው አልነበረም፡፡ ምክንያቱንም ስለምናውቅ ምንም ቅር አላለንም የሱን ማበድና ብቻዉን ማዉራት ባይናችን ስላየን የባሰ እንዳያብድ በማለት በዝምታ አልፈነዋል። ምን ጊዜም ቢሆን እውነትን የተከተለ አሸናፊ እንድሚሆን ስለምናዉቅ ተልባ ቢንጫጫ ብለን አልፈነዋል።
በሌላም በኩል ይኸው ዋና ጸሃፊ የነበረ ግለሰብ ኮምፒተሩ የተበላሸ ጊዜ ያለውን ልናብራራላችሁ እንወዳለን። ኮምፒተሩን ያበላሹት ይመርጡናል ተብሎ እንደገና ለመመለስ እሹሩሩ በመባል ከመቀመጫው ተነስቶ በሁለት እጁ ከሚጨብጣቸው የነጠላ ክርስቲያኖች የማህበረ ሰይጣን አባላት ደጋፊዎቹ ጋር መሆኑን እናዉቅ ነበር። ያደረጉበትም ምክንያት አዲሱ ባይሎው እንዲጸድቅ ስብሰባ በተጠራበት ወቅት በሱና በማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰብ ኮምፒተሩ ከተበላሸ ማን ማን የወር ክፍያ እንደከፈለ የሚያሳይ ሰነድ ስለማይኖር ከፍያለሁ የሚል ሁሉ ገብቶ ባይሎው እንዲሸነፍ እናደርጋለን ተብሎ ታቅዶ እንደነበረና በዚሁም እለት ከፍለው የማያውቁ የማህበረ ሰይጣን አባላት ገብተው መድረኩን እንደሞሉት ባይናችን አይተን ነበር።
ይኸው ዋና ጸሃፊና ተባባሪዎቹ ያላወቁት ኮምፒተር ቢበላሽ (Backup copy) እንደሚኖረው ባለመገንዘባቸው ሰነዱ ሲመጣ ፊታቸው ደም መልበሱንና ምራቃቸው እልዋጥ ሲላቸው እናይ ነበር። በዚሁም ጊዜ ያልከፈላችሁ ሁሉ ዉጡ ሲባል እንወጣም ከፍለናል ብለው ሲከራከሩና ሲሟገቱ በመጨረሻም በፖሊስ ሲወጡ ያላየ የለም። የዋና ጸሃፊው ተንኮልና አሻጥር እስካሁን ወደር አልተገኘለትም። ይህንኑ ተንኮል እያወቅን! ልናጋልጣቸው ያልቻልንበት ምክንያት ያደረጉት ድርጊት ጨለማን ተገን አድርገው ስለነበረ ተባባሪ ባለማገኘታችን ነበር። እንደልማዱ ሚካኤል በዘዴው ጊዜውን ጠብቆ ያዋርዳቸው ብለን ተውነው እንጅ።
ኦዲተር የነበሩትም ወይዘሮ የሰበሰቡትን ገንዘብ እንዴት ኮምፒተር ውስጥ እንዳስገቡ ሲናገሩ ድሮ የቤተክርስቲያኑ ኦዲተር ነበርኩ የሚሉት ግለሰብ ኦዲተር የሆነ የቦርድ አባል እንዴት እገንዘብ ዉስጥ ገብቶ ሊሰበስብ ቻለ ብለው ለመጠየቅ እንኳ አልሞከሩም። ምናልባት እሳቸውም እንዲሁ ያደርጉ ነበር ይሆን? ኦዲተሩ ገንዘብ የሚሰበስብ ከሆነ ማን ኦዲት ሊያደርገው ይሆን? ያለፈው ቅዳሜ ብዙ ሰዎችን አጋልጧል።
የሂሳብ ሹሙና የገንዘብ ባንክ አስገቢው የባንክ ሰነድ ይዘው ብቅ ሲሉ ተዋረድን ብለው አንገታቸውን ደፍተው ራሳቸውን የያዙትን ግለሰቦችን ባይናችን አሳይቶናል። ለመሆኑ እነ አቶ እዩኤል የቤተክርስቲያኑን ሃብት አካተቱ የተባለው ከሰባት መቶ ሽህ ብር በላይ ባንክ የነበረውን አውጥተው በሉ እንጅ የሰንበት ሶስትና ስድስት ሽ ብር በሉ ያለው ማን ይሆን?
አሁንም ለማጣራት የተመረጡት ሰዎች እንዲታገሱና ፕሮፌሽናል የሆኑ ኦዲተሮች ተቀጥረው የወጣዉን ገንዘብ ያህል ወጥቶ ከሳሾቻችን በጠየቁት መሰረት ወደ ኋላ ቢያንስ አስር አመት ጀምሮ አንድ ባንድ እንዲጣራ እንጠይቃለን። ታዲያ አጣሪ ካልሆንኩ ብለው የገቡት አቶ ኪዳኔ ምስክር ምን ሊውጣቸው ይሆን? ያን ሃያ ሺ ለመደለዝ ይሆን የገቡት? ወይስ? ከሳሽ!! እንደገና ተመርማሪ ሆነው ሳለ እንዴት አያፍሩም ሂሳብ ልመርምር ብለው ከመርማሪ ኮሚሽን ጋር ሲሰለፉ? የጉድ ዘመን!!
ድሮ የቤተክርስቲያኑን ሃብት አብረው ካካተቱት ኦዲተር ነበርኩ ከሚሉት ግለሰብ ጋር በመሆን ዘመዳቸዉ የሆኑትን አቶ አለማየሁን የቦርድ ዋና ጸሃፊና የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የቤተክርስቲያኑ ገንዘብ አላፊ፤ ገንዘብ አዉጭና አስገቢ አድርገው በማሾም አብረው የበዘበዙትን እንዲያዉም ቤተክርስቲያኑ የግሌ ነው የሚሉትን አቶ ኪዳኔን መርማሪ ማድረግ አንዱን ሌባ ሌላዉን ሌባ መርምርልኝ የምንል ከሆነ እያወቅን አላዋቂዎች መሆናችን ይመስለናል። ወይም የድሮዎቹን ሌቦች ስም እናድስ ለማለት የተወሰደ ዘዴ እንደሆነ ያሳያል።
ስለዚህ! ባስቸኳይ የታወቁ ፕሮፌሽናል ኦዲተሮች ተከፍለው ወጭውና ገቢው ካለፈው አስር ዓመት ጀምሮ እንዲጣራ እየጠይቅን! አሁንም የተሰበሰበው ቦርድ ካሁን ቀደም በልማድ እንደሚደረገው መጽሃፍ ቅዱስ ጨብጦ ወሬ እንዳይወጣ ከማድረግ ታቅቦ ለቦርድ የቀረበ ጥያቄና የቦርድ ስብሰባ ውጤት በየስብሰባው ቢቻል በማግስቱ ባይቻል በሳምንቱ ለህዝቡ በ http://www.stmichaeleoc.org/index.html እንዲያስታውቁን ጥያቄያችንን እናቀርባለን። ሚካኤል በጥበቡ ቀማኞችን ከቤቱ እንዳስወገደ ሁሉ ለወደፊቱም ቤተክርስቲያናችንን እንዲጠብቅልን አጥብቀን እንጸልይ፡፡
እግዚአብሄር ፍቅርንና ሰላምን ይላክለን!! አሜን!!
Monday, March 1, 2010
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment